ከ87 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መገኘቱን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

36

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ2016 የመስኖ ስንዴ ልማት ሦስት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 120 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱ ይታወሳል፡፡ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌ እና በቤኒሻጉል ጉምዝ ክልሎች እስከ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ሁለት ሚሊዮን 978 ሺህ 122 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል፡፡ ከዚህም ሁለት ሚሊዮን 483 ሺህ 668 ሄክታር መሬት መሰብሰብ ተችሏል፡፡ 1 ሚሊዮን 830 ሺህ 801 ሄክታር በባሕላዊ፣ 652 ሺህ 867 ሄክታር በኮምባይነር የተሰበሰበ ነው፡፡ ከዚህም 87 ሚሊዮን 462 ሺህ 169 ኩንታል ምርት ተገኝቷል።

ከመስኖ ስንዴ ልማቱ ባሻገር በ2016/17 ምርት ዘመን በበልግ አብቃይ በኾኑ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ሶማሌ ክልሎች ሦስት ሚሊዮን 123 ሺህ 797 ሄክታር መሬት ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ከዚህም 81 ሚሊዮን 852 ሺህ 93 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እስከ ግንቦት 01/2016 ዓ.ም ድረስ 3 ሚሊዮን 23 ሺህ 135 ሄክታር መሬት ታርሷል፡፡ 2 ሺህ 639 ሺህ 859 ሄክታር መሬት ደግሞ በዘር ተሸፍኗል፡፡

የግብርና ምርታማነት፣ ጥራት እና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝም የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢትዮጵያን መንግሥት አመሰገነ።
Next articleበሞሮኮ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ሁለንተናዊ ግንኘነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው።