በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢትዮጵያን መንግሥት አመሰገነ።

30

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ ምስጋኑ አረጋ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወካይ የኾኑትን ማርሴል አክፓቮ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮሚሽነሩ ማርሴል አክፓቮ ሥራዎችን ለማከናወን በሚያደርጉት ጥረት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚያደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ እቅዶችን በመተግበር የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር እያደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል። እነዚህ ተግባራትም መንግሥት የዜጎችን መብት ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳዩ አመላክተዋል። ሁለቱ አካላት በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት እንደሚገባም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመላክቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፕል ልማት በሚፈለገው ልክ ምርታማ እንዲኾን ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
Next articleከ87 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መገኘቱን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡