
ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማጅራት ገትር በሽታ ሥርጭት ሰሃል በመባል የሚጠራውን የአፍሪካ ቀጣና የሚያካልል ሲኾን ማሊ፣ ነጀር፣ ቻድ እና ሱዳንን ያካትታል። ወረርሽኙ እሥከ አሁን ድርስ በኒጀር የ143 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፋም ተነግሯል። በሽታው ብዙ ጊዜ ዝናብ በማይኖርበት የበጋ ወራት የሚከሰት ሲኾን ከሕዳር እስከ ግንቦት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያል።
የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለመቆጣጠር በኒጀር ዋና ከተማ እድሜያቸው ከ1 እስከ 19 ዓመት ለሚኾኑ ዜጐች ክትባት እየሠጠ ሲኾን ይህም የበሽታውን ሥርጭት በእጅጉ ይቀንሰዋል የሚል ተሥፋ ተጥሎበታል። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ1996 እሥከ 1997 ባለው ጊዜ ውሥጥ ሰሃል ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካ ክፍል 250 ሺህ የማጅራት ገትር በሽታ የታየ ሲኾን 25 ሺህ የሚሆኑት በኒጀር አካባቢ የሚገኙ መኾናቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!