
ባሕር ዳር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኢክስፖ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ተጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያታምርት ንቅናቄ ያገኘናቸውን ውጤቶች ይበልጥ ማስቀጠል አለብን ብለዋል።
አምራች ኢንደስትሪዎችም በግብዓት፣ በኢነርጂ፣ በገበያ እና በሰው ኃይል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተሻለ ወደ ውጤት ለመለወጥ መትጋት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!