
በኢኮኖሚው ላይ መነቃቃትን እንደሚፈጥር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ። ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ተጀምሯል። ዛሬን ጨምሮ ለስድስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ከአነስተኛ እስከ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች እየተሳተፉ ነው።
የኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በመኾኑ ንቅናቄው በሰፊው መነቃቃትን እንደሚፈጥሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል። ንቅናቄው የጥናት እና ምርምርን፣ ምርትን፣ ግብዓት ማሳደግ እና የማስተሳሰር ዓላማ አለው ብለዋል።
130 ትላልቅ፣ ከ80 በላይ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በኤክስፖው ተሳትፈዋል። ከ300 በላይ የኢንዱስትሪ ትስስርን በመፍጠር 3ቢሊየን ግብይት ይካሔድበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። “በሀገር ውስጥ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች 50 በመቶ ድረስ ምርታቸውን ለሀገር እንዲያቀርቡ በመፍቀድ የጥሬ እቃ እና የገበያ ችግርን እየፈታን ነው” ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!