
ጎንደር: ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የዘጠኝ ወራት የባሕል ግንባታ ዘርፍ ግምገማ በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው። በግምገማ መድረኩ ከፌዴራል እና ከክልሎች የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር መለስ ዓለሙ “የዲሞክራሲን እሴት ለመገንባት እና ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው” ብለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም ችግሮችን በመቋቋም የተለያዩ የሰላም እና ሌሎች ሥራዎች መሠራታቸውን ሚኒስትሩ አንስተዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ግርማ መለሰ (ዶ.ር) የክልሉን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት አቅርበዋል። ኀላፊው በሪፖርታቸው ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የልማት ሥራዎችም እየተከናወኑ መኾናቸውን ጠቅሰዋል። በመድረኩ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው ጎንደርን ጎብኝተው የከተማዋ አምባሳደር እንዲኾኑም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡- አገኘው አበባው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!