“በግብርናው ዘርፍ ያሳካነውን ምርታማነት በኢንዱስትሪው በመድገም ኢኮኖሚያችን ልናሳድግ ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

26

አዲስ አበባ፦ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኢክስፖን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስጀመሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ማግኘት ችለናል ብለዋል።በግብርናው ዘርፍ የመጣው ውጤት ኢንዱስትሪው ካልተዘጋጀ ችግር ይፈጥራል ነው ያሉት። በግብርናው ዘርፍ ስኬት መመዝገቡንም አስረድተዋል።

ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ አንደኛው ግብዓት ነው ይኽንንም በግብርና አሳክተናል፤ ሁለተኛው ኢነርጂ ነው በዓመቱ 12 በመቶ ኢነርጂ አድጓል፤ ሦስተኛው የሰው ኃይል ሲኾን በሁሉም ዘርፍ አስተምረናል። አራተኛው ደግሞ ገበያ ሲኾን የኢትዮጵያ ገበያ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በላይ ነው ብለዋል። እነዚህን በማቀናጀት ኢንዱስትሪውን ማሳደግ ይገባልም ነው ያሉት።

የሀገር ውስጥ ምርትን መጠቀም፤ ምርቱን ለሀገር ውስጥ ተጠቃሚ መቅረብ እንዲሁም መልበስ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በብዙ መንገድ ለኢንዱስትሪ አመች ከባቢ ሁኔታ አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በአግባቡ ተጠቅመን ለውጥ እናመጣለን” ብለዋል።

በኦንላይን ሰበብ ግብር ላለመክፈል የሚደረግ ግብይት ተገቢ አይደለም ብለዋል። በመኾኑም በቂ ግብር ያልሠበሠበ ሰላም እና ፀጥታን ማስከበር እና ኢነርጂን ማቅረብ ስለማይችል እንደሌሎች ሀገራት ግብር በአግባቡ በመሠብሠብ ሀገርን ማሳደግ እንደሚገባም አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የከፈቱት ኤክስፖ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት ይቆያል፡፡

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ የተወሰኑ ኤምባሲዎች በደቦ የሚያወጧቸውን መግለጫዎች እንደማትቀበል ገለጸች።
Next articleማኅበረሰቡን ለግጭት የሚዳርጉ አመለካከቶችን እና አስተሳሰቦችን የመቀየር ሥራ እየተሠራ መኾኑን ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡