ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን ብር በአንድ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶን ለማሠባሠብ እየተሠራ መኾኑ ተገለጸ፡፡

21

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፊታችን እሑድ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን ብር በአንድ ጀምበር በዲጂታል ቴሌቶን ለማሠባሠብ እየተሠራ መኾኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ገልጿል፡፡ በዚህ የዲጂታል ቴሌቶን ላይ ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ዜጎች ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እድል እንደሚፈጥርም ነው ያስገነዘበው።

ጽሕፈት ቤቱ በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚቻልም አመልክቷል። ጽዱ ኢትዮጵያ ግንቦት አራትን ሁሉም እንዲቀላቀልም ጥሪ ቀርቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል በቅርቡ የተሳታፊ ልየታ ሥራ እንደሚጀምር ገለጸ፡፡