
ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የመጪው የክረምት ሥራዎች ትውውቅ መድረክ በጎንደር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። መድረኩ “የዲሞክራሲ እሴት እና ባሕል ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው።
በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የዋናው ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለስ አለሙ፣ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ፣ የፓርቲው የወጣቶች እና ሴቶች ሊግ መሪዎች እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ መሪዎች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!