
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአካባቢው የተገኘውን ሠላም ህብረተሠቡ ማስቀጠል አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ወለጋ ስታድየም በተደረገ ዝግጅት ላይ መኾኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አጋርቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት አለበት ሲሉም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሕዝባዊ ድጋፍ መድረኩ ሠላም፥ አንድነትና የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን ማንሳታቸውንም እንዲሁ።
በአካባቢው የተገኘውን ሠላም ኅብረተሠቡ ማስቀጠል እንደሚኖርበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!