የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ አካል የኾነው የጽዳት እና አረንጓዴ ልማት ሥራ ተጀመረ፡፡

27

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አነሳሽነት የተጀመረው ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ “ጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ አደም ፋራህን ጨምሮ ሚኒስትሮች እንዲሁም ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እግዶች ተገኝተዋል።

ከተሞችን ጽዱ እና በመሠረተ ልማት ያደጉ ለማድረግ እየሠራን ነው ያሉት የከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ለውጡን ለማፋጠን እና የከተሞችን እድገት ለማሳለጥ በተለያዩ ከተሞች ንቅናቄውን በማስፋፋት በሰፊው ይሠራበታል ብለዋል፡፡ በከተሞች ያለው የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት የአካባቢ ሙቀትን በመጨመር የጤና መታወክ እንዲከሰት ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስትሯ ጽዱ የኾኑ ከተሞችን ለመገንባት ንቅናቄውን ዘላቂ ለማድረግ በትጋት እንሠራለን ነው ያሉት፡፡

ከተሞች ጽዱ እንዲኾኑ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድን ለሕዝቡ ለማስገንዘብ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሠራ መኾኑንም ወይዘሮ ጫልቱ ተናግረዋል። በቀጣይም እቅዶች እና ንቅናቄዎች ተግባራዊ እንዲኾኑ ሁሉም የግል እና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ማኅበረሰቡን በማሥተባበር ጽዱ ኢትዮጵያን ሊገነቡ ይገባል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመቀላቀል የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
Next articleበአካባቢው የተገኘውን ሠላም ኅብረተሠቡ ማስቀጠል እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።