
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመቀላቀል የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ኮርፖሬሽኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመደገፍ ነው አስተዋጽኦ ያደረገው።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ውብና ዘመናዊ ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑንም አስታውቋል። የሚገነባቸው ዘመናዊ ሕንጻዎችና የመኖሪያ መንደሮች ውበትን፣ ጥራትንና ዘመናዊነትን ታሳቢ ያደረጉ እንዲኾኑ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የገለጸው ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅንናቄ መሰል ድጋፎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!