“በተሠራው ቅንጅታዊ ሕግ የማስከበር ሥራ በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እየታየ ነው” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ዋለ አባተ

18

ደብረ ማርቆስ: ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ዋለ አባተ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የጸጥታ ኃይል እና ከማኅበረሰቡ ጋር በቅንጅት በሠራው ሕግን የማስከበር ሥራ የዞኑ የሰላም ኹኔታ መሻሻል አሳይቷል ብለዋል፡፡

በዞኑ የነበረው ግጭት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ማስከተሉን የገለጹት ምክትል አሥተዳዳሪው ዞኑን ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኹኔታ ለመመለስ ሰፊ ጥረት መደረጉን አመላክተዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ቢኖሩትም ነፍጥ ማንሳት ግን የከፋ ጉዳት የሚያስከትል ነው፤ ይልቁንም በውይይት ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ አሁንም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል ምክትል አሥተዳዳሪው፡፡ እርስ በእርስ በመጠፋፋት የሚገኝ ውጤት የሌለ መኾኑን በመገንዘብ በዞኑ አሁን ላይ እየታዬ ያለውን አንጻራዊ ሰላም የበለጠ ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት፡፡

ኅብረተሰቡ አሁን ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም አዎንታዊ ሚና መጫወቱንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ካለፈው በመማር አካባቢን ለመጠበቅ እና ሰላምን ዘላቂ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ኅብረተሰቡ እንዲያግዝ ምክትል አሥተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅርን የማጠናከር ተግባራት በልዩ ትኩረት እንደሚፈጸሙም አመላክተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ነቀምቴ ከተማ ገቡ።
Next articleለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዕጩ ምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ እና ዕንባ ጠባቂዎች ምዝገባ 480 ተጠቋሚዎች መመዝገባቸው ተገለጸ፡፡