
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በምሥራቅ ወለጋ ዞን በተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመታደም ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል፡፡
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ አዲስ ከተገነባው የነቀምት አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!