ባሕር ዳር ከተማ ሊገባ የነበረ ሽጉጥ እና ሥናይፐር በቁጥጥር ስር ዋለ።

45

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) መነሻውን ጎንደር ከተማ በማድረግ 51 ኢኮል ሽጉጥ እና አንድ ሥናይፐር ይዞ ወደ ባሕርዳር ከተማ ሊገባ የነበረ ተሽከርካሪ በከተማው የጸጥታ አካላት እና በብሔራዊ የመረጃ ደኅንነት አገልግሎት ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰላም እና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ጌትነት አናጋው ገልጸዋል።

መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ የፌደራል እና የከተማዋ የፀጥታ ተቋማት ተቀናጅተው እየሠሩ መሆኑን መምሪያ ኃላፊው ገልጸዋል። ከተማዋን ከጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ነጻ ለማድረግ በገጠር ቀበሌዎች የተጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት መምሪያ ኃላፊው በዚህም የመንግሥት አገልገሎት እንዲጀመር ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።

በቀጣይም ማኅበረሰቡ የከተማዋን ሠላም ለማረጋገጥ አካባቢውን ተደራጅቶ በመጠበቅ እና የመረጃ ምንጭ በመኾን ኃላፊነቱን እንዲወጣ መልእክት ማስተላለፋቸውን ከባሕርዳር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሠራር ሂደቶችን በመዘርጋት ውጤታማ ሥራዎችን መሥራቱን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Next article“ዛሬ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ሰፋ ያለ መጠነ ርዕይ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)