
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ወረዳዎች በዞኑ ተሰማርቶ ጸጥታ እያሥከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል ለትንሣኤ በዓል መዋያ የሚኾን 37 ሰንጋ በሬዎች እና 16 በጎችን አበርክተዋል።
የዕርድ እንስሳቶቹን የተረከቡት የኮሩ አቅርቦት ኀላፊ ሻምበል ሳሙኤል ታደለ “በሀገሪቱ አራቱ ማዕዘናት በምናደርገው የጸጥታ ማሥከበር ሥራ ሕዝባችን ተለይቶን አያውቅም፤ ዛሬም የትንሣኤ በዓልን እንድናከብር ሕዝቡ ያደረገልን ስጦታ በሠራነው ሥራ የመንፈስ እርካታ እንዲያድርብን ያሥቻለ በመሆኑ ምሥጋናችን የላቀ ነው” ብለዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የጸጥታ ዘርፍ ኀላፊ አበባው አንተነህ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ቀን ከሌሊት ሳይታክቱ መስዕዋትነት ጭምር እየከፈሉ ኅብረተሰቡ በዓሉን እንዲያከብር በማስቻላቸው ክብር አለን ሲሉ ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!