የኢጋድ አባል ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል።

27

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ በጅግጅጋ መካሄድ ይጀምራል፡፡ የኢጋድ አባል ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች ልዑካን በጉባኤ ለመሳተፍ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የገቡ ገብተዋል። ጉባኤው በሸበሌ ወረዳ መካሄድ እንደሚጀምርም ነው የተገለጸው።

ለሁለት ቀናት ቆይታ በሚኖረው በዚህ ጉባኤ የሸበሌ ተፋሰስ ሀገራት የድንበር ተሻጋሪ የከርሰ ምድር ውኃ አጠቃቀም ዙሪያ ምክክር ይደረግበታል ተብሏል። በጉባኤው የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ደብቡ ሱዳን ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮዎች ጨምሮ የዓለም ባንክና ዩኒሴፍ ተወካዮች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕር ዳር ከተማ 25 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የCCTV ካሜራዎችን በድጋፍ አገኘች።
Next articleየዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።