
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለአማራ ክልል ድጋፍ የሰጠውን 25 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የCCTV ካሜራዎች ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አገልግሎት እንዲውል ክልሉ በወሰነው መሰረት ሁሉም ካሜራዎች ተጓጉዘው ባሕር ዳር መግባታቸው ተገልጿል።
የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የክልሉ የከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ቢሮ ለከተማችን ትኩረት በመስጠት ላደረጋችሁት ድጋፍ ከፍ ያለ ምሥጋና እናቀርባለን ብለዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለአማራ ክልል ድጋፍ የሰጠውን 25 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የCCTV ካሜራዎች ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አገልግሎት እንዲውል ክልሉ በወሰነው መሰረት ነው ድጋፉ የተደረገው።
አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ያደረገው ድጋፍ የባሕር ዳር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ በማድረግ ሕዝቡ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ የከተማ አሥተዳደሩን የደኅንነት፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማዘመን ዓላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።
ከተማ አሥተዳደሩ በድጋፍ ያገኛቸው 26 ካሜራዎች በአስር፣ በአምስት፣ በሁለት እና አንድ ኪሎ ሜትር ራዲየስ የሚቀርፁ መሆናቸውንም የባሕር ዳር ከተማ አሥዳደር ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገልጸዋል።
አቶ ጎሹ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የክልሉ የከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ቢሮ ለከተማዋ ትኩረት በመስጠት ላደረጉት ድጋፍ ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ ድጋፉ የከተማውን ደኅንነት ከማስጠበቅ ባለፈ የስማርት ሲቲ ዕቅድን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ የዝርጋታ ሥራውን በማጠናቀቅ እና ወደ ተግባር በማስገባት ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን ሲሉ ከንቲባው ገልፀዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!