የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ለሠራዊቱ የእርድ እንሰሳት ድጋፍ ተደረገ።

29

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ እና አካባቢው ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የትንሣኤን በዓል በማስመልከት የእርድ እንሰሳት ድጋፍ ተደርጓል። በባሕር ዳር ጎንደር ኮማንድ ፖስት ደቡብ ጎንደር ዞን ቀጣና ለተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት ከዞኑ አሥተዳደር እና ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ ሰንጋ በሬዎች፣ በጎች እና ፍየሎች ናቸው ለበዓል መዋያ ስጦታ የተበረከቱት።

ስጦታውን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ እና የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን በቀጠናው ተልዕኮ በመፈፀም ላይ ለሚገኘው የክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል አስማረ አስረክበዋል። መሪዎቹ “ሠራዊታችን የክልላችንን ሰላም ለማረጋገጥ ሌት ተቀን ባደረገው ጥረትና በከፈለው መስዋዕትነት አካባቢያችን የተረጋጋ እንዲኾን አድርጓል፤ ለዚህም ታላቅ ክብር አለን” ብለዋል።

ስጦታውን የተረከቡት ኮሎኔል ሻምበል አስማረ ለሠራዊት ዓባላት ለተደረገው የበዓል ስጦታ አመስግነዋል። ሕገ መንግሥዊ ተልዕኮን በላቀ ብቃት በመፈፀም በክልሉ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም የበለጠ በማጠናከር ሕዝባችንን ወደ ቀደመ ላላሙ እንመልሳለን ሲሉም ተናግረዋል። መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።

Previous articleየአልደፈርባይነት ተጋድሎ!
Next articleባሕር ዳር ከተማ 25 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የCCTV ካሜራዎችን በድጋፍ አገኘች።