የትንሳኤ በዓል በዓለም የምሥራቅ ኦሪዮንታል አብያት ክርስቲያናት አማኞች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

48

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል የምሥራቅ ኦሪዮንታል አብያተ ክርስቲያናትን በሚከተሉ ሀገራት ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉን ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ ሶሪያ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎችም ሀገራት በድምቀት ያከብሩታል፡፡

የጎርጎሮሳውያኑን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት ክርስቲያኖች የትንሳኤ በዓልን ከወር በፊት አክብረዋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኞች (ኦሪዮንታል ኦርቶዶክስ) ዘንድ ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡ የትንሳኤ በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ የጁሊያን ዘመን ቀመርን የሚከተሉ ሀገራት ናቸው በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ሥነ ሥርዓቶች እያከበሩ የሚገኙት፡፡

የዘመን ቀመሯን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጋር አንሰላስላ የምትቆጥረው ኢትዮጵያ የትንሳኤ በዓልን ከሰሙነ ሕማማት ክርስቲያናዊ ሥርዓት በኋላ ዛሬ ጠዋት ጀምራ እያከበረች ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በሚገኙባቸው ሩሲያ፣ ኤርትራ፣ እስራኤል፣ አርመኒያ፣ ሰርቢያ፣ ቤላሩስ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ቡልጋሪያ፣ መቄዶኒያ፣ ጆርጂያ፣ እና ሞልዶቫስ የጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበሩ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ማዕድ አጋሩ።