
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ኅብረት ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። የኅብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የመልካም ምኞት መልዕክት “ለኢትዮጵያውያን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ” ብለዋል።
የትንሳኤ በዓል አዲስ ተስፋን የሚፈነጥቅ የበረከት እና የፍቅር እንዲኾንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲኾን እመኛለሁ ነው ያሉት አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በመልዕክታቸው።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር) እንዲሁ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ የሚል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!