
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “በዓሉ ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የሚነግሥበት እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት የሚጠብቅበት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ” በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ
ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሣዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የትንሣኤውን በዓል ከሞት በኋላ ድኅነት እንዳለ እንዳስተማረን ሁሉ ከፈተናዎቻችን በኋላም ስኬት እንዳለ አውቀን በጽናት እና በአንድነት በመቆም እንዲሁም በዓሉ የደስታ፣ የተስፋ፣ የመታደስ እና የድል አድራጊነት ማሳያ ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ሃጢአት ማስተሰርያ ሲል፣ ክቡር ደሙን አፍስሶ፣ የመስቀልን ሞት/የስቃይን ሞት ሞቶልን፣ ተቀብሮ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል በመንሳት ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ የተነሳበት የትንሳኤው በዓል የደስታ፣ የተስፋ፣ የመታደስ እና የድል አድራጊነት ማሳያ ነውና እኛም ከጥላቻ፣ ከመገፋፋት እና ከመለያየት አስተሳሰብ ተላቀን ስለ ፍቅር እና አንድነት ዘወትር እየተጋን መሆን ይገባል፡፡
በድጋሚ እንኳን ለትንሣዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የሚነግሥበት እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት የሚጠብቅበት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ፡፡
መልካም የትንሣዔ በዓል!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!