ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ፍቅርን፣ መስዋዕትነትን እና ይቅርባይነትን እንማራለን።

57

ደሴ: ሚያዚያ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አስተምኽሮ መሠረት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ ትህትናን እና ይቅር ባይነትን ለማስተማር በሞቱ ሞትን ሽሮ የሰው ልጆችን ለማዳን በቀራኒዮ አደባባይ በራሱ ፍቃድ እንዳለፈ ይገለጻል።

በተለይ በመስቀል ላይ ኾኖ “አባት ኾይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል በሞት መካከልም ኾኖ የይቅርታን ታላቅነት ማስተማሩን እንረዳለን። ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና በስቅለቱ በተግባር ካስተማራቸው ፍቅር እና ትህትና የሰው ልጆች ምን ሊማሩ ይገባል ስንል በደሴ ቅድስት ስላሴ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ተገኝተን በስግደት ላይ ካገኘናቸው ምዕመናን ጋር ቆይታ አድርገን ነበር።

ምዕመናን እንደተናገሩት ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የምንማረው ፍቅርን፣ ራስን አሳልፎ መስጠትን፣ መስዋዕትነትን እና ይቅርባይነትን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ምዕመናኑ አክለውም ሕዝበ ክርስትያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ የተራቡትን በማጉረስ እና በአጠቃላይ በጎ ተግባራትን በማከናወን ሊኾን እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዘጠኝ ሰዓት ሲኾን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየበት ሰዓት ነው፡፡
Next article11 ሰዓት ላይ ከመስቀል ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡