የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች የትንሳዔ በዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።

28

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመምረጥ 190 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ ዱቄት፣ ዘይት፣ ዶሮ፣ እንቁላል እና ብርድ ልብስ ሥጦታ አበርክተናል ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው እማሆይ አበሩ ዓለም ድጋፍ ስለተደረገልኝ ከልመና ወጥቼ በዓሉን በቤቴ በደስታ አሳልፋለሁ። ለረዳችሁኝ ሁሉ እናመሠግናለን ብለዋል። ወይዘሮ ዓለሚቱ ጓንጉል ደግሞ የተደረገላቸው ድጋፍ በዓሉን ከልጆቻቸው ጋር በደሥታ እንዲያሳልፉ እንደሚያደርጋቸው በመግለጽ ድጋፍ ላደረጉላቸው አካላት ምሥጋና አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ የተቋሙ ዋና ተግባር የማስተባበር፣ ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ድጋፍ የሚስፈልጋቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመለየት ለደጋፊዎች ማመቻቸት ነው ብለዋል። በመኾኑም ቢሮው አስቀድሞ በእቅድ በመመራት ጉዳዮን ለሁሉም ዞኖች በማውረድ የድጋፍ ተግባር ተከናውኗል። አፈጻጸሙ ጥሩ ጅምር ነው ብለዋል ኀላፊዋ።

ወይዘሮ ብርቱካን አክለውም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማትን በማሥተባበር መሥራት የሚችሉትን የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት ራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ በመቀየሥ ወደ ሥራ በማሥገባት በኩል ጅምር ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። ኀላፊዋ “ይህ በችግር ውስጥ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማዕድ የማጋራት መልካም እሴት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም” ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ስለ ልጇ አለቀሰች፤ በመከራው አዘነች”
Next articleትንሳዔ እና የእንስሳት አቅርቦት