
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ18 ሺህ ለሚልቁ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለበዓል መዋያ የሚኾን 9 ሚሊየን 833 ሺህ ብር የዓይነት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደረጓል፡፡ ድጋፉ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ፣ ዱቄት፣ ዘይት፣ ዶሮ፣ አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያ እና ሌሎች ለበዓል አስፈላጊ ቁሶችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በድጋፍ ርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር “እየተከናወነ ያለው መተሳሰብ እና መደጋገፍ አንድነትን ያጠናክራል” ብለዋል። ድጋፉ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መኾኑም ተመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!