
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሕዝበ ክርስቲያኑ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣዔ በዓል በሰላም እንዲያከብር ዝግጅት ማጠናቀቁን የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ-ግብረ ኃይል አስታወቀ። በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መግባቱን የጋራ ግብረ-ኃይሉ አስታውቋል፡፡
ሕዝቡም የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን እንዲቆም ጠይቋል፡፡ ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!