ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ።

36

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ ለአቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው መደጋገፍ የእለት ተእለት ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ኢዜአ እንደዘገበው መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የወረዳው ነዋሪዎች የትንሳኤ በዓልን ተደስተው እንዲውሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመሥግነዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleገጣሚው ካሜራ
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ አደም ፋራህ ባሕር ዳር ገቡ።