የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት 374.20 ቢሊዮን ብር መሠብሠቡን ገለጸ።

11

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ሚኒስቴሩ ባለፉት 9 ወራት 391.34 ቢሊዮን ገቢ የመሠብሠብ ግብ አስቀምጦ 374.20 ቢሊዮን ብር መሠብሠቡን ገልጸዋል። ይኽም የእቅዱን 95.62 በመቶ እንደማለት ነው።

አፈጻጸሙ ከባለፈዉ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ43.27 ቢሊዮን ብር ወይም የ25.54 በመቶ ብልጫ ማሥመዝገቡን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ውጤታማ ገቢ አሠባሠብ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኛ ፣ ግብር ከፋዮች ፣ ባለድርሻ አካላት እና የመላው ሕዝብ ሚና ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የገቢዎች ሚኒሰትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።

ተቋሙ የገቢ አሠባሠቡን በየዓመቱ እያሻሻለ የመጣ መሆኑን የጠቋሙት ሚኒሰትሯ ነገር ግን ከመንግሥት የወጪ ፍላጎት፣ የታክስ ገቢ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ጥመርታ አንጻር አፈጻጸሙ ሲመዘን ገና ብዙ መሥራት እንዳለብን ያሣያል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እብሪት እና ትዕቢት ውርደት እና ውድቀት፣ ትህትና ደግሞ ክብረትን ያስገኛል” መምህር ሰናይ አሞኘ
Next articleጸሎተ ሐሙስ እና ጉልባን!