
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ዓለም አቀፉን የሠራተኞች ቀን አክብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላት፣ የሠራተኛ ማኅበሩ አመራሮች እና ሠራተኞች መገኘታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
የሠራተኞች ቀን (ሜይ ዳይ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!