
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የምሁራን እና ወጣቶች ሚና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ውይይቱን ያዘጋጀው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽሕፈት ቤት ሲኾን የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ፈቲ መሃዲ (ዶ/ር) እና ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ወጣት ምሁራንም ተገኝተውበታል።
የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ትውልዱ ከሀገር ተረካቢነት ባለፈ በሀገረ መንግሥት የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በዚህም ሀገርን በሚያሳድጉ ሜጋ ፕሮጀክቶች እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ፈቲ መሃዲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ወጣቱ እንደ ሀገር ኢትዮጵያን ለመገንባት አስተዋጽኦ ሊያደርግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በአፍሪካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን እና አፍሪካን ለመምራት በማሰብ መሥራት ይገባል ነው ያሉት። በውይይት እና በሀሳብ ልዕልና የሚያምን ትውልድ መገንባት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!