የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የትውልድ ቅብብሎሽ የሚጠይቅ መኾኑን ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

31

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሰላም ሚኒሰቴር ከክልል ምክር ቤት፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት እንዲኹም ከክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች ጋር በመኾን በሀገር ግንባታ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይቱ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሰፊ እና የትውልድ ቅብብሎሽ የሚጠይቅ መኾኑን ገልጸዋል። ሂደቱም የማያቋርጥ ውይይት እና ምክክር የሚጠይቅ ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ዜጎች በነጻነት ሃሳባቸውን የሚገልጹበት እና በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት እንዲኾን ምክክሩ ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል።

ብሔራዊ መግባባት የሚጠይቁ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች በመኖራቸው በቂ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማደረግ የሸቀጦች የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስታወቀ።
Next articleባለፉት 9 ወራት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ 1 ቢሊዮን 114 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ።