
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለ2016/17 የምርት ዘመን ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ከውጭ ተጓጉዞ ጂቡቲ ወደብ ደርሷል ተብሏል። ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ 11 ሚሊየን 79 ሺህ 21 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ ነው።
ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም 636 ሺህ 600 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደረሳለች። በተመሳሳይ ከ11 ቀናት በኋላ 543 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።
የግብርና ሚኒስቴር በየዓመቱ እያጠና በሚያቀርበው የሀገሪቱ የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መሠረት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ዓለም አቀፍ ጨረታ እያወጣ የማዳበሪያ ግዥ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!