
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአየር ወለድ እና ኮማንዶ ዕዝ ስር የሚገኝ አንድ ሻለቃ በወሰደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በጽንፈኛው ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ልዩ ስሙ በሬሳና ይድኖ በተባለ ቦታ በተደረገው ሕግ የማስከበር እርምጃ የሕዝቡን ሰላም የሚያረጋግጥ ውጤት መመዝገቡን የሻለቃው አዛዥ ሻለቃ ኢሬና መንገሻ ተናግረዋል።
በተደረገው ሕግ የማስከበር ዘመቻም በርካታ የጦር መሳሪያ እና የፅንፈኛው አባላት መማረካቸውን አዛዡ ገልጸዋል። በወረዳው የተፈጠረው ሰላም ለወረዳው አርሶ አደሮች በሰራዊቱ አጋዥነት የአፈር ማዳበሪያ እስከ ቀበሌ ድረስ እየቀረበ መኾኑን ሻለቃ ኢሬና ተናግረዋል።
የአካባቢው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ይደርስባቸው የነበረው መጉላላት ተቀርፎ እና ካልተገባ ወጪ ተላቀው ወደ እርሻ ሥራቸው እንዲመለሱ ማሥቻሉን ከመከላከከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
