“ለትንሳኤ በዓል እንቅስቃሴ በቂ ተሽከርካሪዎች ወደ ስምሪት እንዲገቡ ተደርጓል” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ጽሕፈት ቤት

19

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ብዙዎች ከቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር በዓሉን ለማሳለፍ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። በዚህም የትራንስፖርት ችግር እንዳይከሰት ከፍተኛ ፍስት ያሉባቸውን መስመሮች በመለየት በቂ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስምሪት በማስገባት አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ አደመ መሰንበት ተናግረዋል።

አቶ አደመ ተጓዦች ለእንግልት እንዳይዳረጉ እና ጤናማ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከባለሃብቶች እና አሽከርካሪ ማኅበራት ጋር ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ በበኩሉ በበዓል ወቅት የሚኖረው የትራንስፖርት ፍሰት ከፍተኛ በመኾኑ አደጋዎችን ለመቀነስ እየሠራሁ ነው ብሏል።

የመንገድ ደኅንነት ትራፊክ ትምህርት እና ሥልጠና ክፍል ኅላፊ ኢንስፔክተር መኮንን ዓለሙ በዓሉን እና በዞኑ ያለውን የጸጥታ ችግር እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ እንዳይደረግ መምሪያው የቁጥጥር ተግባራትን እያከናወነ መኾኑንም ተናግረዋል። በበዓል ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ባለንብረቶችን ጨምሮ አሸከርካሪዎች እና ተጓዦች ተገቢ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነትን ማሳያ መኾኑን አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
Next articleየተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማኅበረሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ።