
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጊቴሬዝ የሶማሊያ ልዩ መልእክተኛ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ልዑክ ዋና ተጠሪ ካትሪወና ላይንግ ጋር ስኬታማ ውይይት አካሂደዋል።
ሚኒስትሩ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አረጋግጠዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቱ ልዩ መልእክተኛዋ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ ላበረከተችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድናቆት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በተጨማሪም ሁለቱ አካላት በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቱ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!