ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትን ለማጠናከር የሚያስችል 165 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አገኘች።

16

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ በዓለም ባንክ አመቻችነት የአረንጓዴ ልማትመርሐ ግብርን ለማጠናከር የሚያስችል165 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አግኝታለች። ከተገኘው ድጋፍ ውስጥም 107 ሚሊዮን ዶላሩ የረጅም ጊዜ ብድር ሲኾን 58 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የልማት ድጋፍ ነው፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ተያያዥ ችግሮችን መቋቋም የምንችለው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት ስንችል ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም በአዲሱ የግብር እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ትኩረት ከተሰጣቸው መስኮች አንዱ መሬትን፣ ደን እና የተፈጥሮ ሃብትን በዘላቂነት በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል። ይህም ለሀገሪቱ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ የፕሮጀክት ታስክ ቡድን መሪ ሚሊዮን ዓለማየሁ በግብርናው ዘርፍ ላይ የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠል በዓለም ባንክ በኩል የሚደረጉ ድጋፎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡ መረጃው የግብርና ሚኒስቴር ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article195 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት መቻሉን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleየሰሜን ጎጃም ኮማንድፖስት በአዴት ከተማ በጽንፈኞች ታግቶ የነበረ የሰባት ዓመት ህጻን አስለቀቀ።