
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ኾኗል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5 ለማኅበራዊ ሳይንስ ሐምሌ 9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።
በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይኾናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!