ትኩረት ሰጥቶ ግብዓት እያሟላ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ገለጸ።

36

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን የሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የሰብል ልማት የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኝ አባተ 231 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ለዘር እየተዘጋጀ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ አምስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱንም አቶ ተገኝ አስታውቀዋል። የታቀደውን ግብ ለማሳካት የግብዓት አቅርቦት ለአርሶ አደሮች እየደረሰ ነው ብለዋል።

ከግብዓት አቅርቦት ባሻገርም ሙያዊ ድጋፍ ይደረጋል፣ እስከ ቀበሌ ድረስ የግንዛቤ ፈጠራ እና የንቅናቄ መድረክም ይካሄዳል ነው ያሉት፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ታምራት ንጋቱ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ግብዓት እያሟላ ነው ብለዋል፡፡ የዞኑ አሥተዳደርም የመኸር ሰብል ልማቱ ስኬታማ እንዲኾን አስፈላጊውን መንግሥታዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፍት መወሰኗን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Next articleየ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ኾነ።