
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፍት መወሰኗን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በኤልሳልቫዶር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌክሳንድራ ሂል ቲኖኮ የተመራው የልዑካን ቡድን ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጋር ተወያይቷል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በውይይታቸው የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን አጠናክረው ለመሥራት የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል። ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፍት መወሰኗን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ሙሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው አምባሳደር ታዬ ለሚኒስትሯ አረጋግጠዋል፡፡
ሁለቱ ሀገሮች በቀጣይ የፖለቲካ ምክክር ለማድረግ በሚያስችሉ እንዲሁም በትምህርት፣ በግብርና፣ በስፖርት እና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመሥራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጀ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!