የጽንፈኛ ቡድኑን ተግባር የማጋለጡ ሥራ ውጤት እያስገኘ መኾኑ ተገለጸ፡፡

19

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን እና በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ እና የኮር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል አዲሱ መሀመድ ጽንፈኛው ቡድን የጥፋት አጀንዳውን ለማሳካት ሕዝቡን በተለያየ ሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያታልል እንደነበር አሰረድተዋል።

አሁን ላይ ግን ሕዝቡ ለአማራ ሕዝብ የማይጠቅም ስበስብ መኾኑን ተገንዝቦ ጽንፈኝነትን ማውገዝ ጀምሯል ብለዋል፡፡ ይህም ጽንፈኛው ከሕዝቡ እንዲነጠል አድርጎታል ብለዋል፡፡ ሠራዊቱ ለሕዝቡ ሰላም ያለመታከት እንደሚሠራና የጥፋት ቡድኑን እግር በእግር ተከታትሎ እርምጃ የመውስድ እና ለሕግ የማቅረብ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የዳንግላ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ጌትነት ማርልኝ በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ስር የሚገኙ ወረዳዎች በክልሉ በተከሰተው የሰላም እና ፀጥታ ችግር ምክንያት የመንግሥት መዋቅሩ መደበኛ ሥራውን አቋርጦ የነበረ መኾኑን አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማኅበረሰቡን በማገልገል ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል ።

ዋና አሥተዳዳሪው ጨምረዉም የተገኘው ሰላም በቀላሉ የመጣ ሳይሆን ሠራዊቱ በከፈለው ውድ ዋጋ በመኾኑ ሕዝቡ የተገኘውን ሰላም ጠብቆ የማቆየት ትልቅ ኀላፊነት አለበት ማለታቸውን ከጎጃም ኮማንድፖስት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢ-ኮሜርስ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
Next article“የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ለአሕጉሩ ድጋፉን እንዲያጠናክር ኢትዮጵያ ጥሪ ታደርጋለች” ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)