
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።
ጉባዔው ማኅበሩ፣ ደጋፊዎች እና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።
የገንዘብ ድጋፍ አቅራቢዎች በ21ኛው የማኅበሩ ዘመን ድጋፋቸውን ለመጨመር በጽኑ እንዲያጤኑ የማሳሰብ ዓላማ ያነገበም ነው።
ድጋፉ የአፍሪካን የልማት ተግዳሮቶች እና መልካም እድሎች በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ አስፈላጊ ነው ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!