ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምስጋና አቀረቡ።

39

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው የዲጂታል ቴሌቶን ለተሳተፉ ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ ብለዋል።

“ለጋራ ጥቅም በጋራ ስንቆም ድንቅ እንኾናለ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ አሁን በጽዱ ኢትዮጵያ ቴሌቶን ያልተሳተፋችሁ በቀሪዎቹ ሰዓታት፣ በመጪዎቹ ቀናት እና ሳምንታትም እንድትቀላቀሉ አበረታታችኋለሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next article“ሰሞነ ህማማቱን ስናስብ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ያለችውን ሀገራችን ኢትዮጵያን በማሰብ ሊኾን ይገባል” የሃይማኖት አባት