ምሥጋና 🙏

16

ዛሬ የምናመሠግናቸው ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው 🙏

🙏 በኢትዮጵያ የዘመናዊ ዲፕሎማሲ ታሪክ ስመ ጥር ናቸው

🙏 ጣልያን ኢትዮጵያን ለመውረር ከሌሎች ሀገራት ጋር ያወጣችውን እቅድ ለማጋለጥ በጊዜው ቅንጣት ታክል ሳይፈሩ ለሀገርና ለወገናቸው ሞግተዋል

🙏 በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የዲፕሎማሲ ሰው የንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የሕግ አማካሪ፣ የባሕል አምባሳደር፣ በወዳጆቻቸው ዘንድ ቅን ሰው ናቸው ይባልላቸዋል

🙏 ስለኢትዮጵያ መሟገት እና ሀገራቸውን በዓለም ዘንድ በበጎ ስሟ እንዲነሳ ማድረግ የጀመሩት ከተማሪነት ጊዜያቸው ጀምሮ ነበር

🙏 ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚያደርጉትን ተጋድሎ በመመልከት በ19 ዓመታቸው የጄኔቫ የኢትዮጵያ ዴሊጌሽን ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ኾነው ተሹመዋል

🙏 በ22 ዓመታቸው በፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል

🙏 ከፈረንሳይ ከተመለሱ በኋላ በተለያዩ ኃላፊነቶች ሀገራቸውን አገልግለዋል

🙏 በኢትዮጵያ ሥራቸውን ሲጀምሩ በምክትል ጽሕፈት ሚኒስትር የጃንሆይ አማካሪ ኾነው ከመሥራት በሻገር የሚኒስትሮችን ሥልጣንና ተግባር በነጋሪት ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲወጣ አድርገዋል

🙏 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመኾን ሀገራቸውን አገልግለዋል

🙏 በኢትዮጵያ የተለያዩ ትልልቅ ተቋማትን ለማቋቋም በርካታ ሥራዎችን ሠርተዋል

🙏 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መመስረትም ዋነኛው ሰው ናቸው

🙏 የሊግ ኦፍ ኔሽን ወደ ዩናይትድ ኔሽን ተቀይሮ ሲቋቋም አብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ነጻ አልወጡም ነበር። በምስረታው ላይ ከአፍሪካ ተሳታፊ ከነበሩት ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ላይቤሪያ ብቻ ነበሩ። አክሊሉ ሀብተወልድም በዩናይትድ ኔሽን ምስረታ ላይ ተገኝተው ቻርተሩ በሚዘጋጅበት ወቅት በኢትዮጵያ በኩል ብዙ አስተዋጽኦ አድርገዋል

🙏 በወቅቱ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በብርቱ ተከራክረው ነበር

🙏 ከጣልያን ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ ለተፈፀመው ግፍ ካሳ ሊከፈል ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል

🙏 ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ባገለገሉበት ወቅትም ለሀገር ሰላም ሲሉ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁ መሪ ነበሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የከፍተኛ መሪዎች ልዑክ ቡድን የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ደሴ ገባ።
Next articleምን ያክል ተዘጋጅተናል?