
አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሁላችንም የምንኮራበት የጋራ ቅርሳችን እና እሴታችን ነው!” በሚል መሪ መልእክት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በአዲስ አበባ በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ይገኛል።
ፊቼ ጫምባላላ ከ9 ዓመታት በፊት የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው። የፊቼ ጫምባላላ በአል ተምሳሌትነቱ ዕርቅና ይቅርታ፣ ሰላምና ፍቅር እንዲሁም አንድነትና መከባበር ነው።
በበዓሉ የክብር እንግዳ ሆነው ከተገኙ መካካል የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም በርካታ ጠቃሚ እሴቶች ያሉትን ይህንን በዓል መጠበቅና መንከባከብ ይገባል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!