በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራ የከፍተኛ መሪዎች ልዑክ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ኮምቦልቻ ገባ።

41

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራ የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ኮምቦልቻ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ኮምቦልቻ ከተማ ሲደርስ በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና በከተማው ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ በቆይታችን በአካባቢው የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል ብለዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮምቦልቻ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል፡፡
በምክትል ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የተመራው ልኡክ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባለፈው ዓመት አርሶ አደሩን ቅሬታ ውስጥ የከተተው የግብዓት እጥረት እንዳይደገም እየተሠራ መኾኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡
Next article“ሀገራት ግጭቶችን በምክክር የፈቱበትን ልምድ እኛም ተግባራዊ ማድረግ አለብን” ፕሬዝዳንት ሳኅለ ወርቅ ዘውዴ