ወደ ሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉዞ ያደረገው የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የልዑክ ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር ምክክር አደረገ።

35

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ልዑኩ በተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች በመዘዋወር ከኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ ከልዩ ልዩ ካምፓኒዎች፣ ከዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማትና አካላት ጋር ውይይት እና ምክክር አድርጓል። በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር የተደረገው ውይይት ደግሞ መንግሥትና ኤምባሲው ማከናወን ስለሚገባቸው የቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና ዲፕሎማቶች የልዑክ ቡድኑ ጋር ባደረጉት ምክክር በቆይታው የተሠራው ሥራ ውጤታማ እንደነበር እና በቀጣይም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስገኘት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት እንደ መነሻ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

በብልጽግና ፖርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር አህመዲን መሐመድ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሪፎርም እና ወቅታዊ የሀገራችንን እና የክልሉን ሁኔታ ለዲፕሎማቶች መረጃ እና ማብራሪያ ሰጥዋል።

የልዑካን ቡድኑ እስካሁን በነበረው ቆይታ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ የሆኑ ተግባራትን ማከናወኑን አውስተው በቀጣይ ከዚህ ጉዞ የተገኙት ተሞክሮዎች ተቀምረው ከትውልደ- ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ፎቶ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋሽንግተን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደሴ ከተማ ነጻ የተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ አገልግሎት እየተሰጠ መኾኑ ተገለጸ፡፡
Next articleአዲስ አበባ የላቀች የዲፕሎማሲ ማእከል ሆና እንድትቀጥል መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።