ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸውን ተቀበሉ።

25

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር ) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሠፈሩት መልእክት “ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸውን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። የቢል እና ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ስርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያለው ነው። ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሠራለን።” ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዓለም ስጋት” አባ ሰንጋ (አንትራክስ)!
Next articleበደሴ ከተማ ነጻ የተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ አገልግሎት እየተሰጠ መኾኑ ተገለጸ፡፡