
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ እና ሌሎችም የክልሉ እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ እና በአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።
የመገጭ መስኖ ፕሮጀክትን የግንባታ እንቅስቃሴ ከተመለከቱ በኃላ በተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በመገኘት የሥራ እንቅስቃሴያቸውን አይተዋል። የምልከታው ዋና ዓላማ የዘርፉን አቅም በመለየት እና የሚገጥሙ ችግሮችን ተደጋግፎ በመፍታት የምርትን መጠን ለማሳደግ ነው።
ከተመለከቷቸው ፋብሪካዎች ውስጥ ዓባይ ጋርመንት ጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ እና ቲቲኬ ዘይት ፋብሪካ ይገኙበታል።
የተጀመሩ ልማቶች እንዲቀጥሉ፣ አዳዲስም እንዲጀመሩ የጎንደርን ከተማ እና የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የበኩላቸውን እየተወጡ የሚገኙ የሰላም አስከባሪ አባላትንም ርእሰ መሥተዳድሩ አበረታተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!