አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሐጂ ባይራም ቬሊ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

24

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአንካራ ሐጂ ባይራም ቬሊ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ወክለው ከአንካራ ሐጂ ባይራም ቬሊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መህመት ናጂ ጋር ስምምነቱን የተፈራረሙት በቱርኪዬ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አደም መሐመድ ናቸው።

የሁለቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስምምነት ዓላማ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር፣ በሥልጠና እና በእውቀት ሽግግር ተባብርው ለመሥራት የሚያስችል ስለመኾኑ ተገልጿል።

መረጃው፡- በአንካራ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ በኾነው “ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል እንድትኾን እየተሠራ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Next articleርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ ያለመ ምልከታ እያደረጉ ነው።