ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የአሜሪካ የማይተካ አጋር መኾኗን አሜሪካ ገለጸች።

42

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የአሜሪካ የማይተካ አጋር መኾኗን አሜሪካ ገልጻለች።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ በሀገራቱ መካከል የዘለቀውን የ120 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባከበረበት ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር እ.አ.አ በሚያዝያ ወር 2023 በአሜሪካ መከላከያ እገዛ አሜሪካዊያን ከሱዳን በሰላም እንዲወጡ ላደረገው አስተዋጽጾ ዕውቅና እንዳለው ገልጿል።

ኢምባሲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ጥረታችን ውስጥ ወሳኝ ነበር፤ በዚህም ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ የማይተካ አጋር ሀገር መኾኑን አረጋግጣለች ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ጎንደር ገቡ።
Next articleየከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።